Amharic Quran

99|1|ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤
99|2|ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
99|3|ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
99|4|በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
99|5|ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
99|6|በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
99|7|የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
99|8|የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

Pages ( 99 of 114 ): « Previous1 ... 9798 99 100101 ... 114Next »