Amharic Quran

86|1|በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
86|2|የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
86|3|ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
86|4|ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
86|5|ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
86|6|ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
86|7|ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
86|8|እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
86|9|ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
86|10|ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
86|11|የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
86|12|(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
86|13|እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
86|14|እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
86|15|እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
86|16|(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
86|17|ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡

Pages ( 86 of 114 ): « Previous1 ... 8485 86 8788 ... 114Next »