Amharic Quran

77|1|ተከታታይ ኾነው በተላኩት፣
77|2|በኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣
77|3|መበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣
77|4|መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣
77|5|መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣
77|6|ምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡
77|7|ያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡
77|8|ከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡
77|9|ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡
77|10|ጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡
77|11|መልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡
77|12|ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤
77|13|ለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡
77|14|የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
77|15|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|16|የፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን?
77|17|ከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡
77|18|በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
77|19|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|20|ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን?
77|21|በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡
77|22|እስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡ መጠንነውም፤ ምን ያማርንም
77|23|መጣኞች ነን!
77|24|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|25|ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን?
77|26|ሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡
77|27|በውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡
77|28|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|29|«ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡
77|30|«ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡
77|31|አጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡
77|32|እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡
77|33|(ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡
77|34|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|35|ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡
77|36|ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡
77|37|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|38|ይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡
77|39|ለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡
77|40|ላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|41|ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
77|42|ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡
77|43|«ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡
77|44|እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
77|45|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|46|ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡
77|47|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|48|«ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡
77|49|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
77|50|ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?

Pages ( 77 of 114 ): « Previous1 ... 7576 77 7879 ... 114Next »