Amharic Quran

93|1|በረፋዱ እምላለሁ፡፡
93|2|በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤
93|3|ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡
93|4|መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
93|5|ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
93|6|የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡
93|7|የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
93|8|ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡
93|9|የቲምንማ አትጨቁን፡፡
93|10|ለማኝንም አትገላምጥ፡፡
93|11|በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡

Pages ( 93 of 114 ): « Previous1 ... 9192 93 9495 ... 114Next »