Amharic Quran

95|1|በበለስና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡
95|2|በሲኒን ተራራም፤
95|3|በዚህ በጸጥተኛው አገርም (እምላለሁ)፡፡
95|4|ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡
95|5|ከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡
95|6|ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡
95|7|ታዲያ ከዚህ በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?
95|8|አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? (ነው)፡፡

Pages ( 95 of 114 ): « Previous1 ... 9394 95 9697 ... 114Next »