Amharic Quran

82|1|ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤
82|2|ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤
82|3|ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤
82|4|መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤
82|5|ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡
82|6|አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?
82|7|በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡
82|8|በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡
82|9|ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡
82|10|በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤
82|11|የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡
82|12|የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡
82|13|እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡
82|14|ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡
82|15|በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡
82|16|እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡
82|17|የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
82|18|ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ?
82|19|(እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡

Pages ( 82 of 114 ): « Previous1 ... 8081 82 8384 ... 114Next »