Amharic Quran

68|1|ነ.(ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡
68|2|አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም፡፡
68|3|ላንተም (ከጌታህ) የማይቋረጥ ዋጋ በእርግጥ አልለህ፡፡
68|4|አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡፡
68|5|ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም፡፡
68|6|ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ፡፡
68|7|ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ተመሪዎቹን ዐዋቂ ነው፡፡
68|8|ለአስተባባዮችም አትታዝዙ፡፡
68|9|ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
68|10|ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡
68|11|ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን፡፡
68|12|ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን፤
68|13|ልበ ደረቅን፣ ከዚህ በኋላ ዲቃላን (ሁሉ አትታዘዝ)፡፡
68|14|የገንዘብና የልጆች ባለቤት በመኾኑ (ያስተባብላል)፡፡
68|15|በእርሱ ላይ አንቀጾቻችን በሚነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡
68|16|በአፍንጫው ላይ በእርግጥ (የሚነወርበት) ምልክት እናደርግበታለን፡፡
68|17|እኛ የአትክልቲቱን ባለቤቶቸ እንደ ሞከርን (የመካን ሰዎች) ሞከርናቸው፡፡ ማልደው (ፍሬዋን) ሊለቅሟት በማሉ ጊዜ፡፡
68|18|(በመሓላቸው) አያስቀሩምም፡፡
68|19|እነርሱ የተኙ ኾነውም ሳሉ ከጌታህ የኾነ ዟሪ በእርሷ ላይ ዞረባት፡፡
68|20|እንደ ሌሊት ጨለማም ኾና አነጋች፤ (ከሰለች)፡፡
68|21|ያነጉም ኾነው ተጠራሩ፡፡
68|22|«ቆራጮች እንደ ኾናችሁ በእርሻቸሁ ላይ ማልዱ» በማለት፡፡
68|23|እነርሱ የሚንሾካሾኩ ኾነው ኼዱም፡፡
68|24|ዛሬ በእናንተ ላይ ድኻ እንዳይገባት በማለት፡፡
68|25|(ድኾችን) በመከልከልም ላይ (በሐሳባቸው) ቻዮች ኾነው ማለዱ፡፡
68|26|(ተቃጥላ) ባዩዋትም ጊዜ «እኛ በእርግጥ ተሳሳቾች ነን» አሉ፡፡
68|27|«ይልቁንም እኛ የተከለከልን ነን» አሉ፡፡
68|28|ትክክለኛቸው «ለእናንተ አላህን ለምን አታጠሩም አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡
68|29|«ጌታችን ጥራት ይገባው፡፡ እኛ በዳዮች ነበርን፤» አሉ፡፡
68|30|የሚወቃቀሱም ኾነው ከፊሎቻቸው በከፊሉ ላይ መጡ፡፡
68|31|«ዋ ጥፋታችን! እኛ ድንበር አላፊዎች ነበርን፤» አሉ፡፡
68|32|«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን (አትክልት) ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ከጃዮች ነን፤» (አሉ)፡፡
68|33|ቅጣቱ እንደዚሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት ታላቅ ነው፡፡ የሚያውቁት በኾኑ ኖሮ (በተጠነቀቁ ነበር)፡፡
68|34|ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው፡፡
68|35|ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን?
68|36|ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ፡፡
68|37|በእውነቱ ለእናንተ በእርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?
68|38|በውስጡ ለእናንተ የምትመርጡት አላችሁ (የሚል)
68|39|ወይስ ለእናንተ የምትፈርዱት አላችሁ በማለት (ቃል ኪዳን የገባንላችሁ) እስከ ትንሣኤ ቀን ደራሽ የኾኑ መሓላዎች ለእናንተ በእኛ ላይ አሏችሁን?
68|40|በዚህ ማንኛቸው ተያያዥ እንደ ኾነ ጠይቃቸው፡፡
68|41|ወይስ ለእነርሱ (በፍርዳቸው ተስማሚ) «ተጋሪዎች» አሏቸውን? እውነተኞችም እንደኾኑ «ተጋሪዎቻቸውን» ያምጡ፡፡
68|42|ባት የሚገለጥበትን (ከሓዲዎች) ወደ መስገድም የሚጥጠሩበትንና የማይችሉበት ቀን (አስታውስ)፡፡
68|43|ዓይኖቻቸው የፈሩ ውርደት የምትሸፍናቸው ሲኾኑ፤ (ወደ ስግደት የሚጠሩበትን)፤ እነርሱም (በምድረ ዓለም) ደህና ኾነው ሳሉ ወደ ስግደት በእርግጥ ይጠሩ ነበሩ፡፡
68|44|በዚህም ንግግር ከሚያስተባብሉት ሰዎች ጋር ተዎኝ፡፡ (እነርሱን እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ ከማያውቁት ስፍራ አዘናግተን እንይዛቸዋለን፡፡
68|45|እነርሱንም አዘገያለሁ፡፡ ዘዴዬ ብርቱ ነውና፡፡
68|46|በእውነቱ ዋጋን ትጠይቃቸዋለህን? ስለዚህ እነርሱ ከዕዳ የተከበዱ ናቸውን?
68|47|ወይስ እነርሱ ዘንድ የሩቁ ምስጢር ዕውቀት አልለን? ስለዚህ እነርሱ ይጽፋሉን?
68|48|ለጌታህም ፍርድ ታገሥ፤ (በመበሳጨትና ባለ መታገሥ) እንደ ዓሣው ባለቤትም (እንደ ዮናስ) አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ (ጌታውን) በተጣራ ጊዜ፡፡
68|49|ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፡፡
68|50|ጌታውም (በነቢይነት) መረጠው፡፡ ከደጋጎቹም አደረገው፡፡
68|51|እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ፡፡ «እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው» ይላሉ፡፡
68|52|ግን እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

Pages ( 68 of 114 ): « Previous1 ... 6667 68 6970 ... 114Next »