Amharic Quran

88|1|የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?
88|2|ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡
88|3|ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡
88|4|ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡
88|5|በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡
88|6|ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡
88|7|የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡
88|8|ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡
88|9|ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡
88|10|በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡
88|11|በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡
88|12|በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡
88|13|በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡
88|14|በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡
88|15|የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡
88|16|የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡
88|17|(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
88|18|ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
88|19|ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
88|20|ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
88|21|አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡
88|22|በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡
88|23|ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤
88|24|አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
88|25|መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡
88|26|ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡

Pages ( 88 of 114 ): « Previous1 ... 8687 88 8990 ... 114Next »