Amharic Quran

111|1|የአቡ ለሀብ ሁለት እጆች ከሰሩ (ጠፉ፤ እርሱ) ከሰረም፡፡
111|2|ከእርሱ ገንዘቡና ያም ያፈራው ሁሉ ምንም አልጠቀመውም፡፡
111|3|የመንቀልቀል ባለቤት የኾነችን እሳት በእርግጥ ይገባል፡፡
111|4|ሚስቱም (ትገባለች)፤ እንጨት ተሸካሚ ስትኾን፡፡
111|5|በአንገትዋ ላይ ከጭረት የኾነ ገመድ ያለባት ስትኾን፡፡

Pages ( 111 of 114 ): « Previous1 ... 109110 111 112113114Next »