Amharic Quran

69|1|እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡
69|2|አረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት!
69|3|አረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
69|4|ሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡
69|5|ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡
69|6|ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡
69|7|ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡
69|8|ለእነርሱም ቀሪን ታያለህን?
69|9|ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡
69|10|የጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡
69|11|እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡
69|12|ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡
69|13|በቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡
69|14|ምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡
69|15|በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡
69|16|ሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡
69|17|መላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡
69|18|በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡
69|19|መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡
69|20|«እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡
69|21|እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡
69|22|በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡
69|23|ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡
69|24|በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡
69|25|መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡
69|26|«ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡
69|27|«እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡
69|28|«ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡
69|29|«ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡
69|30|«ያዙት፤ እሰሩትም፡፡
69|31|«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡
69|32|«ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡»
69|33|እርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡
69|34|ድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡
69|35|ለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡
69|36|ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡
69|37|ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡
69|38|በምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡
69|39|በማታዩትም ነገር፡፡
69|40|እርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡
69|41|እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡
69|42|የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡
69|43|ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
69|44|በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤
69|45|በኀይል በያዝነው ነበር፡፡
69|46|ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡
69|47|ከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡
69|48|እርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡
69|49|እኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡
69|50|እርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡
69|51|እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡
69|52|የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡

Pages ( 69 of 114 ): « Previous1 ... 6768 69 7071 ... 114Next »