Amharic Quran

56|1|መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡
56|2|ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡
56|3|ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡
56|4|ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡
56|5|ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡
56|6|የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ
56|7|ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡
56|8|የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
56|9|የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
56|10|(ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
56|11|እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡
56|12|በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡
56|13|ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
56|14|ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
56|15|በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡
56|16|በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡
56|17|በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡
56|18|ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡
56|19|ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡
56|20|ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡
56|21|ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡
56|22|ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡
56|23|ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡
56|24|በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
56|25|በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡
56|26|ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡
56|27|የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
56|28|በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡
56|29|(ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡
56|30|በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡
56|31|በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡
56|32|ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡
56|33|የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡
56|34|ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡
56|35|እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡
56|36|ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡
56|37|ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡
56|38|ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡
56|39|ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
56|40|ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
56|41|የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡
56|42|በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
56|43|ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
56|44|ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡
56|45|እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡
56|46|በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡
56|47|ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?
56|48|«የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»
56|49|በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡
56|50|«በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡
56|51|«ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!
56|52|« ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡
56|53|«ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡
56|54|«በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡
56|55|«የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
56|56|ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡
56|57|እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
56|58|(በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?
56|59|እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?
56|60|እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
56|61|ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡
56|62|የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?
56|63|የምትዘሩትንም አያችሁን?
56|64|እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
56|65|ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡
56|66|«እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡
56|67|«በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡
56|68|ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?
56|69|እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
56|70|ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
56|71|ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
56|72|እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?
56|73|እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡
56|74|የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
56|75|በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡
56|76|እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡
56|77|እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
56|78|በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
56|79|የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡
56|80|ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
56|81|በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
56|82|ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?
56|83|(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡
56|84|እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡
56|85|እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡
56|86|የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡
56|87|እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡
56|88|(ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡
56|89|(ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡
56|90|ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡
56|91|ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡
56|92|ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡
56|93|ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡
56|94|በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡
56|95|ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡
56|96|የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡

Pages ( 56 of 114 ): « Previous1 ... 5455 56 5758 ... 114Next »