Amharic Quran

91|1|በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡
91|2|በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤
91|3|በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤
91|4|በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤
91|5|በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤
91|6|በምድሪቱም በዘረጋትም፤
91|7|በነፍስም ባስተካከላትም፤
91|8|አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡
91|9|(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡
91|10|(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡
91|11|ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡
91|12|ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡
91|13|ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡
91|14|አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡
91|15|ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡

Pages ( 91 of 114 ): « Previous1 ... 8990 91 9293 ... 114Next »