Amharic Quran

101|1|ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
101|2|ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት!
101|3|ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
101|4|ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤
101|5|ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)
101|6|ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤
101|7|እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡
101|8|ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤
101|9|መኖሪያው ሃዊያህ ናት
101|10|እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
101|11|(እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡

Pages ( 101 of 114 ): « Previous1 ... 99100 101 102103 ... 114Next »