Amharic Quran

78|1|ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?
78|2|ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡
78|3|ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡
78|4|ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
78|5|ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡
78|6|ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?
78|7|ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?
78|8|ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡
78|9|እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡
78|10|ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡
78|11|ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡
78|12|ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡
78|13|አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡
78|14|ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡
78|15|በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡
78|16|የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡
78|17|የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡
78|18|በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡
78|19|ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡
78|20|ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡
78|21|ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡
78|22|ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡
78|23|በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤
78|24|በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡
78|25|ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡
78|26|ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡
78|27|እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡
78|28|በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡
78|29|ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡
78|30|ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡
78|31|ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡
78|32|አትክልቶችና ወይኖችም፡፡
78|33|እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡
78|34|የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡
78|35|በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡
78|36|ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡
78|37|የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡
78|38|መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡
78|39|ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡
78|40|እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡

Pages ( 78 of 114 ): « Previous1 ... 7677 78 7980 ... 114Next »