Amharic Quran

76|1|በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡
76|2|እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡
76|3|እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት)፡፡
76|4|እኛ ለከሓዲዎች ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም አዘጋጅተናል፡፡
76|5|በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
76|6|ከእርሷ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት (ወደፈለጉበት) ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከኾነች ምንጭ (ይጠጣሉ)፡፡
76|7|(ዛሬ) በስለታቸው ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጪ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡
76|8|ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡
76|9|«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡
76|10|«እኛ (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና፤» (ይላሉ)፡፡
76|11|አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው፡፡ (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው፡፡
76|12|በመታገሣቸውም ገነትንና የሐር ልብስን መነዳቸው፡፡
76|13|በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች በውስጧ ፀሐይንም ጨረቃንም የማያዩ ሲኾኑ፡፡
76|14|ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች፣ ፍሬዎችዋም (ለለቃሚዎች) መግገራትን የተገራች ስትኾን (ገነትን መነዳቸው)፡፡
76|15|በእነርሱም ላይ ከብር በኾኑ ዕቃዎች (ሰሐኖች) የብርጭቆዎች በኾኑ ኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል፡፡
76|16|መለካትን የለኳቸው በኾኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)፡፡
76|17|በእርሷም መበረዣዋ ዘንጀቢል የኾነችን ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
76|18|በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ፡፡
76|19|በእነርሱም ላይ (ባሉበት ኹነታ) የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡
76|20|እዚያም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግሥናን ታያለህ፡፡
76|21|አረንጓዴዎች የኾኑ የቀጭን ሐር ልብሶችና ወፍራም ሐርም በላያቸው ላይ አልለ፡፡ ከብር የኾኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ፡፡ ጌታቸውም አጥሪ የኾነን መጠጥ ያጠጣቸዋል፡፡
76|22|«ይህ በእርግጥ ለእናንተ ዋጋ ኾነ፡፡ ሥራችሁም ምስጉን ኾነ፤» (ይባላሉ)፡፡
76|23|እኛ ቁርኣንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው፡፡
76|24|ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ ከእነርሱም ኀጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ፡፡
76|25|የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ፡፡
76|26|ከሌሊቱም ለእርሱ ስገድ፡፡ በረዢም ሌሊትም አወድሰው፡፡
76|27|እነዚያ ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ፡፡ ከባድን ቀንም በስተፊታቸው ኾኖ ይተዋሉ፡፡
76|28|እኛ ፈጠርናቸው፡፡ መለያልያቸውንም አጠነከርን፡፡ በሻንም ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን፡፡
76|29|ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡
76|30|አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡
76|31|የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባዋል፡፡ በዳዮቹንም (ዝቶባቸዋል)፡፡ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡

Pages ( 76 of 114 ): « Previous1 ... 7475 76 7778 ... 114Next »