Amharic Quran

51|1|መበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡
51|2|ከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡
51|3|ገር (መንሻለልን) ተንሻላዮች በኾኑትም (መርከቦች)፡፡
51|4|ነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም (መላእክት) እምላለሁ፡፡
51|5|የምትቀጠሩት (ትንሣኤ) እውነት ነው፡፡
51|6|(እንደየሥራው) ዋጋን ማግኘትም፤ ኋኝ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡
51|7|የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
51|8|እናንተ (የመካ ሰዎች) በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ፡፡
51|9|ከርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል፡፡
51|10|በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡
51|11|እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስሕተተ ውስጥ ዘንጊዎች የኾኑት፡፡
51|12|የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደ ኾነ ይጠይቃሉ፡፡
51|13|(እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው፡፡
51|14|«መከራችሁን ቅመሱ፤ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
51|15|አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
51|16|ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው፤ (በገነት ውስጥ ይኾናሉ)፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና፡፡
51|17|ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡
51|18|በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
51|19|በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡
51|20|በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ፡፡
51|21|በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?›
51|22|ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ውስጥ ነው፡፡
51|23|በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ ነው፡፡
51|24|የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?
51|25|በእርሱ ላይ በገቡና «ሰለም» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡
51|26|ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለ፤» ወዲያውም የሰባ ወይፈንን አመጣ፡፡
51|27|ወደእነርሱም (አርዶና ጠብሶ) አቀረበው፡፡ «አትበሉም ወይ?» አላቸው፡፡
51|28|ከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ «አትፍራ» አሉት፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡
51|29|ሚስቱም እየጮኸች መጣች፡፡ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም፡፡
51|30|እንደዚህ ጌታሽ ብሏል፡፡ «እነሆ እርሱ ጥበባ ዐዋቂ ነውና» አሏት፡፡
51|31|«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው፡፡
51|32|(እነርሱም) አሉ፡- «እኛ ወደ አመጸኞች ሕዝቦች ተልከናል፡፡»
51|33|በእነርሱ ላይ ከጭቃ የኾኑን ድንጋዮች ልንለቅባቸው (ተላክን)፡፡
51|34|በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው) ምልክት የተደረገባት ስትኾን፡፡
51|35|ከምእምናንም፤ በእርሷ (በከተማቸው) ውስጥ የነበሩትን አወጣን፡፡
51|36|በውስጧም ከሙስሊሞች ከአንድ ቤት (ቤተሰቦች) በስተቀር አላገኘንም፡፡
51|37|በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን፡፡
51|38|በሙሳም (ወሬ) ውስጥ ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)፡፡
51|39|ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» አለም፡፡
51|40|እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው፡፡ እርሱ ተወቃሽ ሲኾን በባሕር ውስጥም ጣልናቸው፡፡
51|41|በዓድም በእነርሱ ላይ መካንን ነፋስ በላክን ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡
51|42|በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትኾን እንጂ አትተወውም፡፡
51|43|በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡
51|44|ከጌታቸው ትዕዛዝም ኮሩ፡፡ እነርሱም እያዩ ጩኸት ያዘቻቸው፡፡
51|45|መቆምንም ምንም አልቻሉም፡፡ የሚርረዱም አልነበሩም፡፡
51|46|የኑሕንም ሕዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡
51|47|ሰማይንም በኀይል ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
51|48|ምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች (ነን!)
51|49|ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡
51|50|«ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው)፡፡
51|51|ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና፡፡
51|52|(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡
51|53|በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? አይደለም፤ እነርሱ ጥጋበኞች ሕዝቦች ናቸው፡፡
51|54|ከእነርሱም (ክርክር) ዘወር በል፤ (ተዋቸው)፡፡ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና፡፡
51|55|ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡
51|56|ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
51|57|ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡
51|58|አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡
51|59|ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ (የቅጣት) ፋንታ አልላቸው፡፡ ስለዚህ አያስቸኩሉኝ፡፡
51|60|ለነዚያም ለካዱት ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው፡

Pages ( 51 of 114 ): « Previous1 ... 4950 51 5253 ... 114Next »