Amharic Quran

104|1|ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡
104|2|ለዚያ ገንዘብን የሰበሰበና የቆጣጠረው (ያደለበውም) ለኾነ ፤(ወዮለት)፡፡
104|3|ገንዘቡ የሚያዘወትረው መኾኑን ያስባል፡፡
104|4|ይከልከል፤ በሰባሪይቱ (እሳት) ውስጥ በእርግጥ ይጣላል፡፡
104|5|ሰባሪይቱም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
104|6|የተነደደችው የአላህ እሳት ናት፡፡
104|7|ያቺ በልቦች ላይ የምትዘልቅ የኾነችው፡፡
104|8|እርሷ በእርግጥ በእነርሱ ላይ የተዘጋጀች ናት፡፡
104|9|በተዘረጋች አዕማድ ውስጥ (የተዘጋች ናት)፡፡

Pages ( 104 of 114 ): « Previous1 ... 102103 104 105106 ... 114Next »