Amharic Quran

96|1|አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
96|2|ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
96|3|አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
96|4|ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
96|5|ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
96|6|በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
96|7|ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
96|8|መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
96|9|አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
96|10|ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
96|11|አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
96|12|ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
96|13|አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
96|14|አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
96|15|ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
96|16|ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
96|17|ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
96|18|(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
96|19|ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡

Pages ( 96 of 114 ): « Previous1 ... 9495 96 9798 ... 114Next »