Amharic Quran

83|1|ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡
83|2|ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡
83|3|ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡
83|4|እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን?
83|5|በታላቁ ቀን፡፡
83|6|ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡
83|7|በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡
83|8|ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
83|9|የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡
83|10|ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡
83|11|ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡
83|12|በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡
83|13|አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡
83|14|ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡
83|15|ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡
83|16|ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡
83|17|ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡
83|18|በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡
83|19|ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
83|20|የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡
83|21|ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡
83|22|እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡
83|23|በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡
83|24|በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡
83|25|ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
83|26|ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡
83|27|መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡
83|28|ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡
83|29|እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡
83|30|በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡
83|31|ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡
83|32|ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡
83|33|በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡
83|34|ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡
83|35|በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡
83|36|ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡

Pages ( 83 of 114 ): « Previous1 ... 8182 83 8485 ... 114Next »