Amharic Quran

90|1|በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
90|2|አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
90|3|በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
90|4|ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
90|5|በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
90|6|«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
90|7|አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
90|8|ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
90|9|ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
90|10|ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
90|11|ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
90|12|ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
90|13|(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
90|14|ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
90|15|የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
90|16|ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
90|17|(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
90|18|እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
90|19|እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
90|20|በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡

Pages ( 90 of 114 ): « Previous1 ... 8889 90 9192 ... 114Next »