Amharic Quran

107|1|ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?)
107|2|ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤
107|3|ድኻንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው፡፡
107|4|ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡
107|5|ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡
107|6|ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡
107|7|የዕቃ ትውስትንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)፡፡

Pages ( 107 of 114 ): « Previous1 ... 105106 107 108109 ... 114Next »