Amharic Quran

103|1|በጊዜያቱ እምላለሁ፡፡
103|2|ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፡
103|3|እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡

Pages ( 103 of 114 ): « Previous1 ... 101102 103 104105 ... 114Next »