Amharic Quran

94|1|ልብህን ለአንተ አላሰፋንልህምን? (አስፍተንልሃል)፡፡
94|2|ሸክምህንም ካንተ አውርደንልሃል፡፡
94|3|ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)፡፡
94|4|መወሳትህንም ላንተ ከፍ አድርገንልሃል፡፡
94|5|ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡
94|6|ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
94|7|በጨረስክም ጊዜ ልፋ፡፡ (ቀጥል)፡፡
94|8|ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል፡፡

Pages ( 94 of 114 ): « Previous1 ... 9293 94 9596 ... 114Next »