Amharic Quran

44|1|ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡
44|2|አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡
44|3|እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
44|4|በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
44|5|ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡
44|6|ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
44|7|የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡
44|8|ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡
44|9|በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
44|10|ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡
44|11|ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡
44|12|«ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡
44|13|(ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡
44|14|ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡
44|15|እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡
44|16|ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡
44|17|ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡
44|18|«የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡
44|19|«በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡
44|20|«እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡
44|21|«በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡
44|22|ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡
44|23|(ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡
44|24|«ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡
44|25|ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡
44|26|ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡
44|27|በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡
44|28|(ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡
44|29|ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡
44|30|የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡
44|31|ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡
44|32|ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡
44|33|ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡
44|34|እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡-
44|35|እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡
44|36|እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡
44|37|እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡
44|38|ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡
44|39|ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
44|40|የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡
44|41|ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡
44|42|አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡
44|43|የዘቁመ ዛፍ
44|44|የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡
44|45|እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡
44|46|እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡
44|47|ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡
44|48|ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡»
44|49|«ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡
44|50|«ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
44|51|ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡
44|52|በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
44|53|ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡
44|54|(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
44|55|በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡
44|56|የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡
44|57|ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
44|58|(ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
44|59|ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡

Pages ( 44 of 114 ): « Previous1 ... 4243 44 4546 ... 114Next »