Amharic Quran

70|1|ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡
70|2|በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡
70|3|የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡
70|4|መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡
70|5|መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡
70|6|እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡
70|7|እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡
70|8|ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡
70|9|ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡
70|10|ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡
70|11|(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡
70|12|በሚስቱም በወንድሙም፡፡
70|13|በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡
70|14|በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡
70|15|ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡
70|16|የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡
70|17|(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡
70|18|ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡
70|19|ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡
70|20|ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡
70|21|መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡
70|22|ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡
70|23|እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡
70|24|እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡
70|25|ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡
70|26|እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡
70|27|እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡
70|28|የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡
70|29|እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
70|30|በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
70|31|ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡
70|32|እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡
70|33|እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡
70|34|እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡
70|35|እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡
70|36|ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው?
70|37|ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡
70|38|ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?
70|39|ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡
70|40|በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
70|41|ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
70|42|ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡
70|43|ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡
70|44|ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡

Pages ( 70 of 114 ): « Previous1 ... 6869 70 7172 ... 114Next »