Amharic Quran

1|1|በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
1|2|ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤
1|3|እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ
1|4|የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡
1|5|አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
1|6|ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡
1|7|የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡

Pages ( 1 of 114 ): 1 23 ... 114Next »