Amharic Quran

55|1|አል-ረሕማን፤
55|2|ቁርኣንን አስተማረ፡፡
55|3|ሰውን ፈጠረ፡፡
55|4|መናገርን አስተማረው፡፡
55|5|ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡
55|6|ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡
55|7|ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡
55|8|በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡
55|9|መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡
55|10|ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡
55|11|በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡
55|12|የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡
55|13|(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|14|ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡
55|15|ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡
55|16|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|17|የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡
55|18|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|19|ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡
55|20|(እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡
55|21|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
55|22|ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡
55|23|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|24|እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡
55|25|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|26|በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡
55|27|የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡
55|28|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|29|በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡
55|30|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
55|31|እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡
55|32|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|33|የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)
55|34|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|35|በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡
55|36|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|37|ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡
55|38|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|39|በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡
55|40|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|41|ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡
55|42|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡
55|43|ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡
55|44|በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡
55|45|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|46|በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡
55|47|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|48|የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡
55|49|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|50|በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡
55|51|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|52|በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡
55|53|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|54|የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡
55|55|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|56|በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
55|57|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|58|ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡
55|59|ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|60|የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?
55|61|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|62|ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡
55|63|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›
55|64|ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡
55|65|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|66|በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡
55|67|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|68|በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡
55|69|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|70|በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡
55|71|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|72|በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
55|73|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|74|ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡
55|75|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?
55|76|በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡
55|77|ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
55|78|የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡

Pages ( 55 of 114 ): « Previous1 ... 5354 55 5657 ... 114Next »