Amharic Quran

92|1|በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡
92|2|በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡
92|3|ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡
92|4|ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡
92|5|የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡
92|6|በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤
92|7|ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
92|8|የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤
92|9|በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤
92|10|ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
92|11|በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡
92|12|ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡
92|13|መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡
92|14|የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡
92|15|ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡
92|16|ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡
92|17|አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡
92|18|ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡
92|19|ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡
92|20|ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡
92|21|ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡

Pages ( 92 of 114 ): « Previous1 ... 9091 92 9394 ... 114Next »