Amharic Quran

81|1|ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
81|2|ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
81|3|ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤
81|4|የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤
81|5|እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤
81|6|ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
81|7|ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤
81|8|በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
81|9|በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤
81|10|ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
81|11|ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
81|12|ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
81|13|ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
81|14|ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
81|15|ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡
81|16|ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡
81|17|በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
81|18|በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡
81|19|እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡
81|20|የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡
81|21|በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡
81|22|ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
81|23|በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡
81|24|እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡
81|25|እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡
81|26|ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?
81|27|እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
81|28|ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡
81|29|የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡

Pages ( 81 of 114 ): « Previous1 ... 7980 81 8283 ... 114Next »