Amharic Quran

80|1|ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡
80|2|ዕውሩ ስለ መጣው፡፡
80|3|ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡
80|4|ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡
80|5|የተብቃቃው ሰውማ፤
80|6|አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡
80|7|ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡
80|8|እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤
80|9|እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤
80|10|አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡
80|11|ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡
80|12|የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡
80|13|በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡
80|14|ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡
80|15|በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡
80|16|የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡
80|17|ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው?
80|18|(ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?)
80|19|ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡
80|20|ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡
80|21|ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡
80|22|ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡
80|23|በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡
80|24|ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡
80|25|እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡
80|26|ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤
80|27|በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤
80|28|ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤
80|29|የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤
80|30|ጭፍቆች አትክልቶችንም፤
80|31|ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡
80|32|ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡
80|33|አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤
80|34|ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤
80|35|ከናቱም ካባቱም፤
80|36|ከሚስቱም ከልጁም፤
80|37|ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡
80|38|ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤
80|39|ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡
80|40|ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤
80|41|ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤
80|42|እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡

Pages ( 80 of 114 ): « Previous1 ... 7879 80 8182 ... 114Next »