Amharic Quran

87|1|ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
87|2|የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
87|3|የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
87|4|የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
87|5|(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
87|6|(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
87|7|አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
87|8|ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
87|9|ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
87|10|(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡
87|11|መናጢውም ይርቃታል፡፡
87|12|ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡
87|13|ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡
87|14|የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡
87|15|የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡
87|16|ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
87|17|መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡
87|18|ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡
87|19|በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡

Pages ( 87 of 114 ): « Previous1 ... 8586 87 8889 ... 114Next »