Amharic Quran

100|1|እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
100|2|(በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
100|3|በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
100|4|በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
100|5|በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡
100|6|ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
100|7|እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡
100|8|እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡
100|9|(ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤
100|10|በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡
100|11|ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡

Pages ( 100 of 114 ): « Previous1 ... 9899 100 101102 ... 114Next »