Amharic Quran

75|1|(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡
75|2|(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
75|3|ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?
75|4|አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡
75|5|ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡
75|6|«የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡
75|7|ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡
75|8|ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡
75|9|ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡
75|10|«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡
75|11|ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡
75|12|በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
75|13|ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡
75|14|በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡
75|15|ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡
75|16|በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡
75|17|(በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡
75|18|ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡
75|19|ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡
75|20|(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡
75|21|መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡
75|22|ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡
75|23|ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡
75|24|ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡
75|25|በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡
75|26|ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤
75|27|«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡
75|28|(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡
75|29|ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡
75|30|በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡
75|31|አላመነምም አልሰገደምም፡፡
75|32|ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡
75|33|ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡
75|34|የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡
75|35|ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡
75|36|ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?
75|37|የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
75|38|ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡
75|39|ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡
75|40|ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?

Pages ( 75 of 114 ): « Previous1 ... 7374 75 7677 ... 114Next »