Amharic Quran

102|1|በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡
102|2|መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡
102|3|ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡
102|4|ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡
102|5|በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡
102|6|ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡
102|7|ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡
102|8|ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡

Pages ( 102 of 114 ): « Previous1 ... 100101 102 103104 ... 114Next »