Amharic Quran

84|1|ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
84|2|ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
84|3|ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
84|4|በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
84|5|ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
84|6|አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
84|7|መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
84|8|በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
84|9|ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
84|10|መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
84|11|(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
84|12|የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
84|13|እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
84|14|እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
84|15|አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
84|16|አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
84|17|በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
84|18|በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
84|19|ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
84|20|የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
84|21|በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
84|22|በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
84|23|አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
84|24|በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
84|25|ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡

Pages ( 84 of 114 ): « Previous1 ... 8283 84 8586 ... 114Next »