Amharic Quran

97|1|እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡
97|2|መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
97|3|መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
97|4|በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
97|5|እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡

Pages ( 97 of 114 ): « Previous1 ... 9596 97 9899 ... 114Next »