Amharic Quran

85|1|የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
85|2|በተቀጠረው ቀንም፤
85|3|በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
85|4|የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
85|5|የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
85|6|እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
85|7|እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
85|8|ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
85|9|በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
85|10|እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
85|11|እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
85|12|የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
85|13|እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
85|14|እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
85|15|የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
85|16|የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
85|17|የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
85|18|የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
85|19|በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
85|20|አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
85|21|ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
85|22|የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡

Pages ( 85 of 114 ): « Previous1 ... 8384 85 8687 ... 114Next »