Amharic Quran

37|1|መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡
37|2|መገሠጽንም በሚገሥጹት፤
37|3|ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡
37|4|አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው፡፡
37|5|የሰማያትና የምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው፡፡ የምሥራቆችም ጌታ ነው፡፡
37|6|እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡
37|7|አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት፡፡
37|8|ወደላይኛው ሰራዊት አያዳምጡም፡፡ ከየወገኑም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፡፡
37|9|የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፡፡ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው፡፡
37|10|ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር፤ (እርሱ ይሰማዋል)፡፡
37|11|ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው? (ፍጡር) እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው፡፡
37|12|ይልቁንም (በማስተባበላቸው) ተደነቅህ፤(ከመደነቅህ) ይሳለቃሉም፡፡
37|13|በተገሠጹም ጊዜ አይመለሱም፡፡
37|14|ተዓምርን ባዩም ጊዜ ለመሳለቅ ይጠራራሉ፡፡
37|15|ይላሉም «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
37|16|«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
37|17|«የቀድሞዎቹ አባቶችንም? (ይላሉ)፡፡
37|18|«አዎን እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)» በላቸው፡፡
37|19|እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ እነርሱም ወዲያውኑ (ምን እንደሚፈጸምባቸው) ያያሉ፡፡
37|20|«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው» ይላሉም፡፡
37|21|«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉ የነበራችሁት መለያው ቀን ነው» (ይባላሉ)፡፡
37|22|(ለመላእክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ይግገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) ሰብስቡ፡፡
37|23|«ከአላህ ሌላ (የሚገዙዋቸውን ሰብስቧቸው) ወደ እሳት መንገድም ምሩዋቸው፡፡
37|24|«አቁሟቸውም፡፡ እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና» (ይባላል)፡፡
37|25|(ለእነርሱም) «የማትረዳዱት ለእናንተ ምን አላችሁ? (ይባላሉ)፡፡
37|26|በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ወራዳዎች ናቸው፡፡
37|27|የሚወቃቀሱም ሆነው ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ይመጣሉ፡፡
37|28|(ለአስከታዮቹ) እናንተ ከስተቀኝ ትመጡብን ነበር ይላሉ፡፡
37|29|(አስከታዮቹም) ይላሉ «አይደለም ፈጽሞ ምእምናን አልነበራችሁም፡፡
37|30|«ለእኛም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም፡፡ በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ሕዝቦች ነበራችሁ፡፡
37|31|«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠብን፤ እኛ (ሁላችንም ቅጣቱን) ቀማሾች ነን፡፡
37|32|«ወደ ጥምመት ጠራናችሁም፡፡ እኛ ጠማሞች ነበርንና» (ይላሉ)፡፡
37|33|ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ነጋሪዎች ናቸው፡፡
37|34|እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡
37|35|እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡
37|36|እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን? ይሉም ነበር፡፡
37|37|አይደለም እውነቱን (ሃይማኖት) አመጣ፡፡ መልክተኞቹንም እውነተኛነታቸውን አረጋገጠ፡፡
37|38|እናንተ አሳማሚውን ቅጣት በእርግጥ ቀማሾች ናችሁ፡፡
37|39|ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም፡፡
37|40|ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች (ቅጣትን አይቀምሱም)፡፡
37|41|እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አላቸው፡፡
37|42|ፍራፍሬዎች (አሏቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው፤
37|43|በድሎት ገነቶች ውስጥ፡፡
37|44|ፊት ለፊት የሚታያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡
37|45|ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡
37|46|ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከኾነች፡፡
37|47|በእርሷ ውስጥም ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡
37|48|እነርሱም ዘንድ ዓይናቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች የኾኑ ዓይናማዎች አልሉ፡፡
37|49|እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) ዕንቁላል ይመስላሉ፡፡
37|50|የሚጠያየቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ፡፡
37|51|ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል «እኔ ጓደኛ ነበረኝ፡፡
37|52|«በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን? የሚል፡፡
37|53|«በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡
37|54|እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡
37|55|ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡
37|56|ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡
37|57|«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡»
37|58|(የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን?
37|59|«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡
37|60|ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
37|61|ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡
37|62|በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
37|63|እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል፡፡
37|64|እርሷ በገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡
37|65|እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡
37|66|እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡
37|67|ከዚያም ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከተኳሳ ውሃ ቅልቅል (መጠጥ) አልላቸው፡፡
37|68|ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው፡፡
37|69|እነሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋልና፡፡
37|70|እነሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና፡፡
37|71|ከእነርሱ በፊትም የቀድሞዎቹ (ሕዝቦች) አብዛኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል፡፡
37|72|በውስጣቸውም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል፡፡
37|73|የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
37|74|ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
37|75|ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን!
37|76|እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን፡፡
37|77|ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን፤
37|78|በርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልካም ዝናን) ተውን፡፡
37|79|«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑሕ ላይ ይኹን፡፡»
37|80|እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
37|81|እርሱ ከምእምናን ባሮቻችን ነውና፡፡
37|82|ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡
37|83|ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡
37|84|ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡፡
37|85|«ለአባቱና ለሕዝቦቹ ምንን ትግገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ፡፡
37|86|«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
37|87|«በዓለማትም ጌታ ሃሳባችሁ ምንድን ነው?» አለ፡፡
37|88|በከዋክብትም መመልከትን ተመለከተ፡፡
37|89|«እኔ በሽተኛ ነኝም» አለ፡፡
37|90|ከእርሱም የሸሹ ሆነው ኼዱ፡፡
37|91|ወደ አማልክቶቻቸውም ተዘነበለ፡፡ አለም፡- «አትበሉምን?»
37|92|«የማትናገሩት ለናንተ ምን አላችሁ?»
37|93|በኀይል የሚመታቸውም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ፡፡
37|94|ወደእርሱም (ሰዎቹ) እየሮጡ መጡ፡፡
37|95|አላቸው «የምትጠርቡትን ትግገዛላችሁን?»
37|96|«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን፡፡»
37|97|«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ፡፡
37|98|በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው፡፡
37|99|አለም «እኔ ወደ ጌታዬ ኼያጅ ነኝ፡፡ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡»
37|100|ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡
37|101|ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡
37|102|ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
37|103|ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡
37|104|ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
37|105|ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
37|106|ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡
37|107|በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡
37|108|በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡
37|109|ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡
37|110|እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
37|111|እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው፡፡
37|112|በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡
37|113|በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን፡፡ ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሠሪ አልለ፡፡ ለነፍሱ ግልጽ በዳይም አለ፡፡
37|114|በሙሳና በሃሩን ላይም በእርግጥ ለገስን፡፡
37|115|እነርሱንም ሕዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን፡፡
37|116|ረዳናቸውም፡፡ እነርሱም አሸናፊዎች ነበሩ፡፡
37|117|በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው፡፡
37|118|ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው፡፡
37|119|በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው፡፡
37|120|ሰላም በሙሳና በሃሩን ላይ ይሁን፡፡
37|121|እኛ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡
37|122|ሁለቱም በእርግጥ ከአመኑት ባሮቻችን ናቸው፡፡
37|123|ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
37|124|ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፤ አላህን አትፈሩምን?
37|125|በዕልን ትገዛላችሁን? ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?
37|126|አላህን ጌታችሁንና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁን ጌታ (ትተዋላችሁን)?
37|127|አስተባበሉትም፡፡ ስለዚህ እነርሱ (ለቅጣት) የሚጣዱ ናቸው፡፡
37|128|ንጹሕ የተደረጉት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ፡፡
37|129|በእርሱ ላይም በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት፡፡
37|130|ሰላም በኢልያሲን ላይ ይሁን፡፡
37|131|እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡
37|132|እርሱ በእርግጥ ከምእመናን ባሮቻችን ነው፡፡
37|133|ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
37|134|እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳንናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡
37|135|(በቅጣቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር፡፡
37|136|ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡
37|137|እናንተም ያነጋችሁ ስትሆኑ በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ (በቀን) ታልፋላችሁ፡፡
37|138|በሌሊትም (ታልፋላችሁ)፤ ልብም አታደርጉምን?
37|139|ዩኑስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡
37|140|ወደ ተመላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
37|141|ዕጣም ተጣጣለ፡፡ ከተሸነፉትም ሆነ፡፡
37|142|እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳው ዋጠው፡፡
37|143|እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነም ኖሮ፤
37|144|እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡
37|145|እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው (በባሕር) ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡
37|146|በእርሱም ላይ (በአጠገቡ) ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን፡፡
37|147|ወደ መቶ ሺሕ ሰዎችም (ዳግመኛ) ላክነው፡፡ ከቶውንም ይጨምራሉ፡፡
37|148|አመኑም፡፡ እስከ ጊዜ ድረስም አጣቀምናቸው፡፡
37|149|(የመካን ሰዎች) ጠይቃቸውም፡፡ «ለጌታህ ሴቶች ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራልን?»
37|150|ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?
37|151|ንቁ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው (የተነሳ) ይላሉ፡-
37|152|«አላህ (መላእክትን) ወለደ፡፡» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡
37|153|በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶችን ልጆች መረጥን?
37|154|ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
37|155|አትገነዘቡምን?
37|156|ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጅ አላችሁን?
37|157|«እውነተኞች እንደ ሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)፡፡
37|158|በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ፡፡ አጋንንትም እነርሱ (ይህን ባዮች በእሳት) የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ ዐውቀዋል፡፡
37|159|አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
37|160|ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)፡፡
37|161|እናንተም የምትገዟቸውም ሁሉ፤
37|162|በእርሱ (በአላህ) ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም፡፡
37|163|ያንን እርሱ ገሀነምን ገቢ የሆነውን ሰው ቢሆን እንጅ፡፡
37|164|(ጂብሪል አለ) ከእኛም አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ፡፡
37|165|እኛም (ጌታን ለመግገዛት) ተሰላፊዎቹ እኛ ነን፡፡
37|166|እኛም (አላህን) አጥሪዎቹ እኛ ነን፡፡
37|167|እነርሱም (ከሓዲዎቹ) በእርግጥ ይሉ ነበሩ፡-
37|168|«ከቀድሞዎቹ (መጻሕፍት) ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረን ኖሮ፤
37|169|«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር፡፡»
37|170|ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ካዱ፡፡ ወደፊትም በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
37|171|(የእርዳታ) ቃላችንም መልክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች፡፡
37|172|እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
37|173|ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
37|174|ከእነርሱም (ከመካ ከሓዲዎች) እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር (ተዋቸው)፡፡
37|175|እያቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያያሉ፡፡
37|176|በቅጣታችንም ያቻኩላሉን?
37|177|በቀያቸውም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
37|178|እነርሱንም እስከ (ጥቂት) ጊዜ ድረስ ተዋቸው፡፡
37|179|ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ፡፡
37|180|የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
37|181|በመልክተኞቹም ላይ ሰላም ይኹኑ፤
37|182|ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፡፡

Pages ( 37 of 114 ): « Previous1 ... 3536 37 3839 ... 114Next »